እንደሌሎቹ ቅመማ ቅመሞች እርድም ለዘመናት ለባህላዊ ህክምና ጥቅም ላይ ሲውል ነበር
ይሄ ቅመም ለምግብ ማጣፈጫነት ብቻ ሳይሆን ለሰውነት መቆጣትን እና የሰውነታችን ሴሎች ወደ ካንሰርነት እንዳይቀየሩ ያደርጋል እንዲሁም ለልብ በሽታ መከላከል በትልቁ ያግዛል
ለእርድ ቢጫ መልክ እንዲኖረው የሚያደርገው ዋነኛ ኬሚካል ኩርኩሚን ይባላል:: ይሄ ንጥረ ነገር ከላይ ከጠቀስናቸው ቁሰስስትን ከመከላከል በተጨማሪ የማርጀት ሁደትን ይቀንሳል ፣ የመርሳት በሽታም እንዳይከሰት ያደረርጋል
ምንም እንኳ እርድ እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም ከተመገብነው በኋላ ቶሎ ወደ ደመማችን ስለማይዋሃድ አንድ ጊዜ ተመገበነው ውጤት መጠበቅ አይኖርብንም፡፡ በተደጋጋሚ መጠቀምና ከተገኘ የቫይታሚን እንክብሎችን መውሰድ ይገባናል፨
የእርድ ሳይንሳዊ ጥቅሞች
1. እርድ የሰውነት መቆጣት ወይም ቁስለትን ይከላከላል
በሰውነታችን በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ ቁስለቶችን ለማዳን ይረዳል፨ እንደሁም አንድ ቆየት ያለ ጥናት እንደሚያሳየው እርድ በትክክለኛው መጠን ከተወሰደ ከአስፕሪንና አድቪል የተሻለ ኢንፌክሽኖችን እና ቁስለትን ያሽላል፨
2. እርድ የልብ በሽታን ይከላከላል
እርድ የልብን የውስጠኛውን የልብ ሽፋን ስራ በማቀላጠፍ የደም ዝውውረን ያሻሽላል፨ የዚህ ኢንዶተሊያል ተብሎ የሚጠራው የልብ አካል ስራ ሲቀንስ የእርጅና መጠን ይጨምራል እንዲሁም የልብ በሽታ ተጋላጭነት ይጨምራል፨ ስለሆነም እርድ እድሜ ማርጀት ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችልን የልብ በሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል
አንድ ጥናት የ8 ሳምንታት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከእርድ እንክብሎች ውጤት ጋር በማነፃፀር ያገኘው ውጤት እንደሚያሳየው ሁለቱም የልብን ስራ በማጎልበት ረገድ ተመሳሳይ ውጤት እንዳላቸው ነው፨
ሌላ ጥናት ደግሞ ለሁለተኛው አይነት የስኳር ታማሚዎች እርድ ሊፒቶር የሚባለው ለልብ ድካምና ስትሮክ መከላከያ ከሚሰጠው መድሃኒት እኩል ጥቅም እንደሚሰጥ ነው
3. እርድ ካንሰርን ለመከላከልና ምናልባትም ለማከም ያግዛል
እርድ ኢንፌክሽኖችን እና ቁስለትን ስለሚከላከል ከተለያዩ አይነት ካንሰሮችን ለመከላከል ያግዛል፨ ለምሳሌ የአንጀት፥የጣፊያ፥የፕሮስቴት፥የጡት እና የጨጓራ ካንሰር ይከላከላል ተብሎ ይታመናል፨
አንድ በአይጦች ላይ ተሞክሮ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው በእርድ ውስጥ የሚገኘው ኩርኩሚን የሚባለው ንጥረ ነገር የካንሰር እጢዎች እንዳይፈጠሩ ከተፈጠሩም እንዳይስፋፉ ያደርጋል ፨ ጥናቱ በሰዎች ላይ እየተሞከረ ይገኛል፨
4. እርድ የስኳር በሽታን ለመከላከልና ለማከም ይረዳል
ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶችን በማየት የተገኘ ድምዳሜ እንደሚያሳየው ኩልኩሚን የስኳር በሽታን ለማከምና ለመከላከል ያግዛል በተጨማሪም ከስኳር በሽታ ጋር የተገናኘ የኩላሊት በሽታን ይከላከላል፨ ሆኖም ጥናቶቹ ባብዛኛው የተደረጉት በእንስሳት ላይ ነው ፨
የስኳር በሽተኛ በሆኑ አይጦች ላይ የተሞከረ ጥናት እንደሚያሳየው ኮልኩሚን ለውጥ መልኩ የደም ስኳራቸውን ቀንሷል
5. እርድ የመርሳት በሽታን ቶሎ እንዳይከሰት ወይም እንዲዘገይ ያደርጋል
እርድ በጭንቅላት እና ስፓይናል ኮርድ የሚገኘው የነርቭ አጠቃላይ ጤናን የሚጠብቅ ፕሮቲንን በመጨመር የአዕምሮ ዝግመት በሽታን ይከላከላል፨
6. እርድ ድብርትን ይከላከላል
ልክ እንደ የመርሳት በሽታ እርድ የአዕምሮ ስራን ያቀላጥፋል፨ እንደ ፀረ-ድብርት ያገለግላል፨
አንድ ጥናት አይጦችን ለ10 ቀናት ኮርኩሚን በመውጋት የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው እርድ ድብርትን የመከላከል አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ነው
እንደ አኤአ 2014 ላይ የታተመ ጥናት 60 የድብርት በሽታ ተጠቂዎችን በ3 በመክፈል ፣ለ1ዱ ግሩፕ የተለመደውን የድብርት መድሃኒት ፥ለ2ኛው ግሩፕ የእርድ እንክብል ፥ ለ3ኛው ግሩፕ ደግሞ የሁለቱን ውህድ የተሰጣቸው ሲሆን ፣ በስድስተኛው ሳምንት ሁሉም ተመሳሳይ ለውጥ ማምጣት ችለዋል፨
7. እርድ ሰውነታችንን ከሚበክሉ ነገሮች ይከላከላል
ከአካባቢ ብክለት፥ ከሲጋራ ጭስ ፥እንዲሁም የፋብሪካዎች ኬሚካል ሰውነታችን ለረጅም ጊዜ ሲጋለጥ ለካንሰር ፥ ለልብ በሽታ ፥ የመርሳት በሽታ ከመሳሰሉት በሽታዎች እንጋለጣለን ። ። ። እርድ ሰውነታችን ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ይቀንሳል
8. እርድ እርጅናን ይከላከላል
ከላይ በጠቀስናቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ምክንያት የአዕምሮን ጤና በመጠበቅ እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን ይከላከላሉ፨
9. እርድ የአይን ጤናን ይጠብቃል
እአአ 2018 በScientific Reports የታተመ ጥናት እንደሚያሳየው እርድ የአየዕን ጤናን ከመጠበቅ አንፃር እስከ 23 በመቶ መሻሻል አሳይቷል፨
ግላኮማ ለአይነ ስውር ከሚዳርጉ በሽታዎች ዋነኛው ነው፨
ከላይ ከጠቀስናቸው ጥቅሞች በተጨማሪ እርድ ለደም ግፊት በሽታ፥ ለቦርጭ መከላከያነት ይውላል
ጥቅሞቹን ለማግኘት ዘወትር ግማሽ የሻይ ማንኪያ እርድ በሻይ መልክ ብንጠቀም ይመከራል
እርድ መጠቀም የሌለባቸው ሰዎች
1 የኩላሊት ወይም የአሞት ጠጠር ህመም ያለባቸው ሰዎች
2 ቃር ያለባቸው ሰዎች
3 ቀዶ ጥገና የሚያደርጉ ሰዎች
4 ደም ማነስ ያለበት ሰው
5 እርጉዝ ሴቶች እርድን እንዲጠቀሙ አይመከርም
ከዚህ ቀጥሎ እርድን ለውበት እንዴት እንደምንጠቀም
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ