የደም ግፊት በሽታን
ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚረዱን ምግቦች
የደም ግፊት በሽታ ምንነት
ደም ግፊት ማለት በሰውነታች የሚገኙ የደም ቧንቧዎች
ላይ ያለው ጫና ወይም ግፊት ማለት ነው፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊት የደም ማስተላለፊያ ቧንቧዎች መጎዳትን በማስከተል ለልብ በሽታ፣ለኩላሊት
እና ለስትሮክ ሊዳርገን ይችላል፡፡ደም ግፊት በእንግሊዘኛው ሳይለንት ኪለር ወይም በአማርኛ ዝምተኛው ገዳይ ተብሎ ይጠራል፡፡ ምክንያቱም…
ሳይታወቅ ለረዥም ጊዜ ስለሚቆይ ነው፡፡
ለደም ግፊት ብዙ አጋላጭ ምክንያቶች አሉ ለምሳሌ እድሜ፣የቤተሰብ
ታሪክ፣ፆታ እና ዘር ሲሆኑ ሆኖም በአመጋገብና በሰውነት እንቅስቃሴ ልንቆጣጠረው እንችላለን፡፡
በፖታሺየም፣ማግዚዢየም ፣ፋይበርና አነስተኛ ሶዲየም መጠን
ባላቸው ምግቦች የደም ግፊትን እንደሚቀንሱ ይታመናል፡፡ ምክንያቱም በቂ ፖታሺየም መውሰድ በጨው ውስጥ ያለውን ንጥረነገር ሶዲየም
ስለሚቀንስ ነው፡፡
ቀጥሎ የደም ግፊትን ለማስተካከል የሚረዱንን ምግቦች እንመለከታለን፡፡
1. ነጭ ሽንኩርት
ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ነጭ ሽንኩርት የናይትሪክ ኦክሳይድ መጠንን በመጨመር የደም ግፊትን ይቀንሳል፡፡
ናይትሪክ ኦክሳይድ የደም ቧንቧዎችን ያፍታታል፡፡
2. አጃ
አጃ ከፍተኛ መጠን ፋይበር፣ዝቅተኛ ስብ እና ሶዲየም ስላለው የደም ግፊትን ይቀንሳል፡፡
3. አቮካዶ
አቮካዶ በውስጡ ከፖታሺየም በተጨማሪ ለደም ግፊት መቀነስ የሚያግዘውን ማግኒዚየም የያዘ ነው፡፡ አንድ
አቮካዶ 549ሚሊ ግራም ፖታሺየም ይይዛል
4. እርጎ
እርጎ ከፍተኛ መጠን ያለው ካልሺየም ስለያዘ ደም ግፊትን ለመቀነስ ያግዛል፡፡ በሳምንት ከ5 ጊዜ ያላነሰ
እርጎ መጠቀም የደም ግፊት ተጋላጭነትን በ20 በመቶ ይቀንሳል፡፡
5. ሙዝ
አንድ መካከለኛ መጠን ያለው ሙዝ 400ሚሊግራም ፖታሺየም እና 1ሚሊግራም ሶዲየም ይይዛል፡፡ ከፍተኛ
ፖታሺየምና ዝቅተኛ ሶዲየም ለደም ግፊት መቀነስ ቀጥተኛ አስተዋፆ አለው
6. ብርትኳን
ብርትኳን ቫይታሚን ሲ ይዘቱ በጣም የሚታወቅ ሲሆን በተጨማሪም ፖታሺየም የይዛል ፡፡ አንድ ብርተኳን 326ሚሊግራም ፖታሺየም እና ዚሮ ሶዲየም ይዘት አለው፡፡
7. ወይን ፍሬ
Bioflaninoid የሚባል በወይን ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ለደም ግፊት መቀነስ ጠቃሚ ነው፡፡
በሩብ ኪሎ ወይን ውስጥ 166ሚሊግራም ፖታሺየም አለው፡፡
8. ሐባብ
ሃባብ በውስጡ ከፍተኛ መጠን ያለው ፖታሺየም ስለያዘ ለደም ግፊት ቁጥጥር እጅግ ያግዛል፡፡ በተጨማሪም
ሃባብ ቫይታሚን ኤ እና ሲ ይይዛል፡፡
ደም ግፊት ካለብን ማስወገድ የሚገባን ምግቦችና መጠጦች
የተለያዩ ምግቦች የደም ግፊታችንን በመጨመር ለአደጋ ሊዳርጉን ይችላሉ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብን ልናስወግዳቸው የሚገቡ ናቸው
1. ጨው
ጨው በያዘው የሶዲየም መጠን ምክንያት ለልብ እና ለደም
ግፊት በሽታ ሊዳርግ ይችላል፡፡
በትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት
የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች በቀን ውስጥ የሚወስዱትን የጨው መጠን 1500ሚሊገራም ወወይም ከአንድ የሻይ ማንኪየ በታች መሆን አለበት፡፡
የምንወስዳቸው ጨው ከምግብ ቤቶች ፣ከታሸጉ ምግቦች እና
ከመሳሰሉት ስለሆነ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
2. ስኳር
ስኳር ከመጠን ያለፈ ክብደት እንደሚያስከትል ይታወቃል፡፡
ግን በተጨማሪም የደም ግፊት በሽታም መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡
በተለይ የስኳር ማጠፈጫ የተጨመረባቸው መጠጦች መጠቀም
ለከፍተኛ ክብደት መጨመር ከዛም ለደም ግፊት ይዳርጋል
የአሜሪካ የልብ ማህበር በቀን ውስጥ የምንጠቀመው የስኳር
መጠን ከ6-9 የሻይ ማንኪያ መብለጥ እንደሌለበት ያስጠነቅቃል፡፡
3. የታሸጉ ምግቦች
የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ሳቹሬትድ ፋት እና ትራንስ
ፋት በብዛት ያለባቸውን ምግቦች መመገብ አይገባቸውም፡፡ ለምሳሌ የዶሮ ቆዳ፣ቀይ ስጋ እና ቅቤ የመሳሰሉ ናቸው
በተጨማሪም የተጠቀሱት የስብ አይነቶች ኮልስትሮል መጠንን
ከፍ በማድረግ ለከፍተኛ የልብ በሽታ ይዳርጋሉ
ይሄንን ለመከላከል የእንስሳት ስብን እንደ ኦሊቭ ዘይት
፣አቮካዶ እና ለውዝ በመሳሰሉ በእፅዋት ስብ መተካት ያስፈልጋል
4. አልኮል መጠጥ
በጣም አነስተኛ መጠን አልኮል መጠጥ የደም ግፊትን እንደሚቀንስ
ቢታመንም አብዝቶ መጠጥ ማዘውተር ግን በተቃራኒው ለደም ግፊት እና ካንሰር ይዳርጋል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ