የተዛባ የወር አበባ ዑደት ለሚያጋጥማቸው ሴቶች ፍቱን መፍትሄዎች

 

የተዛባ የወር አበባ ዑደት ለሚያጋጥማቸው ሴቶች ፍቱን መፍትሄዎች


አንዲት ሴት በአማካይ በየ24-38 ቀናት የወር አበባ ታያለች፡፡ ከ2 እስከ 8 ቀናት ሊቆይ ይችላል፡፡

የተዘበራረቀ የወር አበባ ዑደት ማለት

-        ወርሃዊው የወር አበባ መከሰቻ ጊዜ ሲቀያየር

-        ብዙ ወይም በጣም ትንሽ ደም ሲፈስ

-        የወር አበባ ተከስቶ የሚቆይበት ቀናት መቀያየር ሊሆን ይችላል

የተዘበራረቀ የወር አበባ ዑደት መከሰት ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው;

ብዙ ምክንያቶች ለምሳሌ የኦርሞን መቀያየር እና እድሜ የወር አበባ ዑደትን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡

ሌሎች ዋና ዋና ምክንያቶች ሊሆኑ የሚችሉ

-        የእርግዝና መከላከያ ሉፕ

-        የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መቀያየር

-        ከባድ የሰውነት እንቅስቃሴ

-        እርግዝና ወይም ጡት ማጥባት

-        ሃይፐር ታይሮይዲዝ

-        ማህፀን ግድግዳ ላይ እብጠት ወይም መወፈር

-        እና ሌሎች

የወር አበባ ዑደትን የሚያስተካክሉ ቤት ውስጥ በቀላሉ ሊገኙና ሊዘጋጁ የሚችሉን ከነጥቅማቸው እንመለከታለን

1.       የተፈጨ ቀረፋ

ቀረፋ የሰውነትን ሙቀት እንደሚጨምር ይታመናል፡፡ ይሄም በመሆኑ ከፔሬድ ጋር ተያይዞ ለሚያጋጥም ህመም ማስታገሻነት ፣የተዘበራረቀ ፔሬድ  ለሚያዩ እህቶች እና ለተቆጣ ሰውነት ማስታገሻነት መፍትሄ ይሆናል፡፡

አዘገጃጀት

1.       በአንድ ሲኒ ውስጥ የተፈጨውን ቀረፋ ዱቄት ይክተቱት

2.      ውሃ ጨምረው በደንብ ያማስሉት

3.      ከ10 ደቂቃ በኋላ ቲባግ ይጨምሩበትና ለ3ደቂቃ ያስቀምጡት

4.      አንድ ማንኪያ ስኳር ወይም ማር ጨምረው በየቀኑ ይጠጡት

 

2.      በደንብ ያልበሰለ ፓፓያ

በደንብ ያልበሰለ ፓፓያ የሰውነት መቆጣትን የመከላከል አቅም ስላለው በፔሬድ ጊዜ የሚያጋጥምን ህመም ያስታግሳል፡፡ በተጨማሪም የጡንቻ እና የማህፀን ግድግዳዎችን  መሳሰብን የሚያረጋጉ እንደ አይረን፣ካሮትን ፣ካልሺየም እና ቫይታሚን ሲ እና ኤን ይዟል፡፡

አዘገጃጀት

1.       ፔሬድ ከማየትዎ ሁለት ቀን በፊት ፓፓያውን ያዘጋጁ

2.      በትናንሹ ይቆራርጡት እና ከእርጎ ጋር ይደባልቁተ

3.      በቁርስ መልክ ወይም እንደመክሰስ ይመገቡት

3.      የተፈጨ እርድ

የወር አበባ ዑደትን እና የሰውነታችንን ኦርሞኖ ባላንስ በማስተካከል እርድ ወደር የለውም ፡፡ የሰውነት መቆጣትን እና በወር አበባ ወቅት የሚያጋጥምን ህመም ያስታግሳል፡፡

አዘገጃጀት

1.       ሩብ የሻይ ማንኪያ እርድ በብርጭቁ ያድርጉ

2.      አንድ ማንኪያ ማር እና ወተት አንድ ላይ ይቀላቅሉ

3.      በየቀኑ ይጠጡት

4.      ቁንዶ በርበሬ

ቁንዶ በርበሬ የወር አበባ ዑደት መዛባትን እና ህመምን ያስታግሳል

አዘገጃጀት

1.       2የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ (ያልተፈጨ) በአንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ ይጨመሩ

2.      ሌሊቱን እንዲዋሃድ ያስቀምጡት

3.      ጠዋት ጠዋት አጥልለው ይጠጡት

 

5.      ፐርስሊ (የሾርባ ቅጠል)

ፐርስሊ አፒዮል የሚባል ንጥረ ነገር ስለያዘ የወር አበባ ዑደትን በማስተካከልና በማመጣጠን ትልቅ ስራ ይሰራል

 

በየቀኑ የፐርስሊ ጁስ መጠጣት ለጤናማ የወር አበባ ዑደት ያግዛል

አዘገጃጀት

1.       ፐረስሊውን በጁስ መፍጫ ይፍጩት

2.      በብርጭቆ ይቅዱትና ጣፋጭ ነገር ይጨምሩበት

3.      በየቀኑ የጠቀሙት

 

 

የወር አበባ ስለጤናችን የሚጠቁመውን 4 ነገሮች

1.       የወር አበባ የሆድ ቁርጠት

በታችኘው የሆድ ክፍል ከባድ ቁርጠት ያስከትላል

የማህፀን ግድግዳዎች መቁሰል ሊያመላክት ይችላል

ከባድ የጤና ችግር ጠቋሚ ምልክት ነው

2.      የወር አበባ ቀለም

ቀይ ቀለም ካለው ትክክለኛው ሲሆን ሆኖም የተጋገረ እና ሰማያዊ መሰል፣ፒንክ፣ኢንጆሪ ቀለም ያለው የወር አበባ የማህፀን በተለያዩ ምክንየቶች መወፈር ሊያመላክት ይችላል

3.      የወር አበባ አፈሳሰስ ሁኔታ

በወር አበባ ወቅት ከፍተኛ የደም መፍሰስ ከተከሰተ የደም ማነስ፣የማህፀን ግድግዳ መቁሰል፣የማህፀን በር ላይ እጢ እንዲከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል

4.      የወር አበባ ከሄደ በኋላ ድጋሚ መከሰት

የወሊድ መቆጣጠሪያ እየወሰዱ ከሆነ ችግር የለውም ሆኖም ምንም አይነት መቆጣጠሪያ ሳይጠቀሙ ይሄ የተከሰተ ከሆነ ባፋጣኝ ሀኪምዎን ያማክሩ፡፡

 

 

አስተያየቶች

  1. እነመሠግነለን ግን የኦርሞን ችግር አለብኝ እነ መድሀኒት ምንም ለዉጥ የለም ምን ትመክሩኝ አላቹህ የወር አበባ ሊመጣ ሞት አፉፍ ደርሸ እመለሣለሁ 3ቀነት

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

አስተያየት ይለጥፉ