ኩላሊታችንን የሚጎዱ 7 ምግብና መጠጦች

የመኪና እጥበት ግዜ ከቧንቧው የሚመጣው ከፍተኛ ግፊት ያለው ውኃ መኪናው ላይ ያለውን ቆሻሻዎች ያስወግዳል፡፡ የኩላሊት ስራም እንደዛ ነው መርዛማ ነገሮችን ከደማችን በሽንት መልክ ማስወገድ ኩላሊቶቻችን ከ200ሊትር በላይ ደም ያጣራል ከዛ ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑትን 20ሊትር በላይ ያስወግዳል በኀል የለ ቅዳሜ የለ እሁድ የለ 24 ሰዓታት ስራ ላይ ነው ደግነቱ ቆሻሻዎቹን ቢያስወግዱም ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በደማችን ውስጥ ያስቀርልናል ይህን የሰውነታችን አካል ጤና መጠበቅ ለሰውነታችን የሚያስፈልጉ መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ስለዚህ ማንኛቸውም የምንመገባቸውም ሆነ የምንጠጣቸው ነገሮች የኩላሊታችን ጤና ላይ ትልቅ ተፅእኖ አላቸው በተከታታይ የምንመገባቸው ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችና መጠጦች ኩላሊታችን ላይ ጫና ያሳድራል ፣ እኛንም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል መልካሙ ዜና ግን ፣ ኮላሊት ችግር ያለበት እንኳ ቢሆን አመጋገብን ለማስተካከል ግዜው አልረፈደም በዚህ ቪዲዮ ኩላሊታችን ለተለያ 7 አይነት ምግቦችና መጠጦች የሚያሳየውን ሪአክሽን እንመለከታለን 1. ቀይ ስጋ ፕሮቲን ለሰውነታችን አስፈላጊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ግን ማር ሲበዛ ይመራል እንደሚባለው … ለምሳሌ ቀይ ስጋ ብዙ የእንስሳት ፕሮቲን የያዘ ስለሆነ ኩላሊታችንን በጣም ይጎዳል ምክንያቱመ ፡- ኩላሊታችን ይህንን ፕሮቲን ለይቶ ማውጣት እና ለሰውነታችን የሚጠቅመውን መለየት ይኖርበታል እነዚህ የበዙ ፕሮቲኖች ወደ ሰውነታችን ሲገቡ ኩላሊታችን ጫናውን መቋቋም ያቅተዋል ኩላሊታችን አላስፈላጊ ነገሮች ማስወገድ ሲያቅታቸው ፣ አሲዳማ ዝቃጮች ይከማቻል ለሰውነታችን ትክክለኛ የሆነውን ምግብ መምረጥ ይገባል ቀይ ስጋ መመገብ ለኩላሊታችን መጥፎ አልኮልም እንደዛው ነው፡፡ የኩላሊታችንን የማጣራት ስራ ከባድ ያደርገዋል በተጨማሪም ብዙ መጠጥ ሰውነታችን ውስጥ ያለውን የውኃ መጠን ይቀንሰዋል ያ ማለት፡- የሰውነታችን አካለት በቂ ውኃ ካላገኙ በተገቢው ስራቸውን ማከናወን አይችሉም በሰውነታችን ያለውን የፈሳሽ መጠን ለማመጣጠን ሶዲየም እንደሚያስፈልጋችው ይታወቃል፡፡ ብዙ ጨው ግን ኩላሊታችን ብዙ ውኃ እንዲይዝ ያደርገዋል ፣ በሽንት መልክ ብዙ ፕሮቲን እንዲወገድ ያደርጋል እነዚህ በሀገራችን በብዛት የሚዘወተሩት እንደ ቡና እና ሻይ ያሉ መጠጦች ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች ናችው እንዚህ መጠጦች ኩላሊታችንን ስራውን በከፍተኛ ፍጥነት እንዲያከናውን ያስገድዱታል አነቃቂ ንጥረ ነገሮቹ የደም ዝውውርን ያፋጥናሉ ፣የደም ግፊትን ይጨምራሉ ሌላም ተፅእኖ አላቸው ልክ እንደጨው የሰውነታችንን የውኃ መጠን ይቀንሳሉ ያም ለኩላሊት ጠጠር ሊዳርግ ይችላል፡፡ በቀን ውስጥ ከ2 ሲኒ ቡና በላይ መጠጣት ወተት እና የወተት ተዋፅኦ የፕሮቲን ምንጮች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በልኩ መወሰድ ይገባቸዋል፡፡ በተለይ የኩላሊት ችግር ላለበት ሰው ምክንያቱ፡- ብዙ ወተት እና የወተት ተዋፅኦ መውሰድ የካልሺየም መጠንን በሽንት መልኩ እንዲወገድ በማድረግ ለኩላሊት ጠጠር ይዳርጋሉ፡፡ ኩላሊት ከልክ በላይ ሲሰራ፣ሊወገድ የሚገባውን ፕሮቲን መቆጣጠር ስለማይችል በአደገኛ መጠን ሊጨምር ይችላል ኩላሊታችን ሲታመም ለሰውነታችን በየቀኑ የማያስፈልጉ እና ሊወገዱ የሚገባቸውን ፎስፈረስ ማስወገድ አይችሉም፡፡

አስተያየቶች